ሕዝባዊ በዓል · የኦርቶዶክስ በዓል

ጥምቀት

Epiphany (Timkat)

የጥምቀት በዓል በክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የሚያስታውስ ደማቅ በዓል ነው።

ቀጣይ ቀንጥር 11, 2019 ዓ.ምማክሰኞ, ጃንዩወሪ 19, 2027
67ቀናት ቀርተዋል
Priests in ceremonial robes carrying the tabots on their heads at Timket

በየዓመቱ ያሉ ቀኖች

ሁሉም በዓላት
ዓመትየኢትዮጵያ ቀንየግሪጎሪያን ቀን
2018ጥር 11ሰኞ, ጃንዩወሪ 19, 2026
2019ጥር 11ማክሰኞ, ጃንዩወሪ 19, 2027
የሚመጣው ጥምቀት ማክሰኞ, ጃንዩወሪ 19, 2027 ነው፣ ከ67 ቀን በኋላ።
2020ጥር 11ሐሙስ, ጃንዩወሪ 20, 2028
2021ጥር 11ዓርብ, ጃንዩወሪ 19, 2029
2022ጥር 11ቅዳሜ, ጃንዩወሪ 19, 2030
2023ጥር 11እሑድ, ጃንዩወሪ 19, 2031
2024ጥር 11ማክሰኞ, ጃንዩወሪ 20, 2032
2025ጥር 11ረቡዕ, ጃንዩወሪ 19, 2033
2026ጥር 11ሐሙስ, ጃንዩወሪ 19, 2034

ታሪክ

የጥምቀት በዓል በክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የሚያስታውስ ደማቅ በዓል ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት ታሪክ የሚገኘው በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፫ ቁ ፲፫–፲፯ ውስጥ ነው።

አከባበር

ጥር 10 ቀን፣ ታቦታት ከየአቢያተ ክርስቲያናቱ በዓሉ ወደሚከበርበት ቦታ በምዕመናን ታጅበው እየዘመሩ ይሄዳሉ። እዚያም በየተዘጋጀው ድንኳን እንዲያርፉ ተደርጎ ሌሊቱን እዛው ያሳልፋሉ። ብቦታውም፣ በገጠር ወራጅ ውሃ ይከተራል በከተሞች ደግሞ ሰው ሰራሽ ግድብ ይሰራል። ጥር 11 ቀን የጥምቀት ዕለት፤ ጎኅ ሲቀድ ምእመናን እዚያው በድንኳኑ ዙሪያ አስቀድሰው ሲጨርሱ በካህናት መሪነት ሁሉም ወደከተራው ያመራና ውሃውም ተባርኮ ሕዝቡ ይረጫል። ከዚህ ሥነ ሥርዓት በኋላ በመቋሚያ፣ በከበሮና በጽናፅል በሚታጀብ ኃይማኖታዊ ዝማሬ፣ ወንዱ በሆታ፤ ሴቱ በእልልታ፤ ካህኑ በሃሌታ ታቦተ ሕጉን አጅበው፣ እንደያመጣጣቸው ወደየ ቤተክርሲያናቸው ይመለሳሉ።

ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች

Timkat is on Tir 11, usually January 19. The next one is ጃንዩወሪ 19, 2027 (ጥር 11, 2019 ዓ.ም).

ተዛማጅ