የኢትዮጵያ በዓላት
ሕዝባዊ፣ የኦርቶዶክስ፣ የእስልምና እና ባህላዊ በዓላት። ዓመትና ዓይነት ይምረጡ፣ ከዚያም ታሪኩንና ቀኖቹን ለማየት ማንኛውንም በዓል ይክፈቱ።
| ስም | አይነት | ቀን | |
|---|---|---|---|
| እንቁጣጣሽ እንቁጣጣሽ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ሲሆን የሚከበረውም በመስከረም 1 ነው። | ሕዝባዊ በዓልየስራ ዕረፍት | መስከረም 1ዓርብ, ሴፕቴምበር 11, 2026 | ዝርዝር |
| መስቀል መስቀል በ4ኛው ክፍለ ዘመን በእቴጌ እሌኒ አማካኝነት እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለብትን መስቀሉ መገኘት አስመልክቶ የሚከበር ዓመታዊ በዓል ነው። በመስከረም 17 የሚከበር ሲሆን፣ በጣም ከደመቁት እና በቀለማት ያሸበረቁት የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በዓላት ዉስጥ አንዱ ነው። | ሕዝባዊ በዓልየኦርቶዶክስ በዓልየስራ ዕረፍት | መስከረም 17እሑድ, ሴፕቴምበር 27, 2026 | ዝርዝር |
| ገና ገና ታኅሣሥ 29 (በ 4 ዓመት አንዴ ታኅሣሥ 28) ቀን ይከበራል። | ሕዝባዊ በዓልየኦርቶዶክስ በዓልየስራ ዕረፍት | ታኅሣሥ 29ሐሙስ, ጃንዩወሪ 7, 2027 | ዝርዝር |
| ጥምቀት የጥምቀት በዓል በክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የሚያስታውስ ደማቅ በዓል ነው። | ሕዝባዊ በዓልየኦርቶዶክስ በዓልየስራ ዕረፍት | ጥር 11ማክሰኞ, ጃንዩወሪ 19, 2027 | ዝርዝር |
| የዓድዋ ድል በየካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአጼ ምኒልክ በተመራው የኢትዮጵያ ሠራዊትና ባህር አቋርጦ ከአውሮፓ ከመጣው የጣሊያን ሠራዊት ጋር የተካሄደው የዓድዋው ጦርነት በታሪክ ውስጥ ከሚጠቀሱ ጉልህ ክስተቶች መካከል አንዱ ነው። | ሕዝባዊ በዓልየስራ ዕረፍት | የካቲት 23ማክሰኞ, ማርች 2, 2027 | ዝርዝር |
| ኢድ አል-ፈጥር ኢድ አል-ፈጥር "የጾም መፍቻ በዓል" ማለት ሲሆን፣ ከሁለቱ ዋና ዓመታዊ የእስልምና በዓላት አንዱ ነው። የረመዳን ወር የ29 ወይም የ30 ቀናት ጥብቅ ጾም ማብቃቱን ያበስራል። | ሕዝባዊ በዓልየእስልምና በዓልየስራ ዕረፍት | የካቲት 30ማክሰኞ, ማርች 9, 2027 * | ዝርዝር |
| ስቅለት ስቅለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ፣ መሰቀልና በጎልጎታ ላይ የሞተበትን ዕለት የምታስብበት ታላቅ የሕማም፣ የሐዘንና የንስሐ ቀን ነው። | ሕዝባዊ በዓልየኦርቶዶክስ በዓልየስራ ዕረፍት | ሚያዝያ 22ዓርብ, ኤፕሪል 30, 2027 | ዝርዝር |
| የሰራተኞች ቀን የሰራተኞች ቀን፣ ወይም ዓለም አቀፍ የሰራተኞች ቀን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበር ሲሆን በኢትዮጵያም በሚያዝያ 23 ይከበራል። ይህ የሕዝብ በዓል የሰራተኞችን አስተዋጽኦ እና ስኬቶች እንዲሁም የሰራተኞች ንቅናቄን ያወሳል። | ሕዝባዊ በዓልየስራ ዕረፍት | ሚያዝያ 23ቅዳሜ, ሜይ 1, 2027 | ዝርዝር |
| ፋሲካ (ትንሳኤ) ፋሲካ (ትንሳኤ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ እጅግ ታላቅና ዋናው በዓል ነው። ይህ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ መነሳቱን የሚያከብር ሲሆን፣ ለሰው ዘር ሁሉ የተሰጠውን የተስፋና የዘላለም ሕይወት ድል ያበስራል። | ሕዝባዊ በዓልየኦርቶዶክስ በዓልየስራ ዕረፍት | ሚያዝያ 24እሑድ, ሜይ 2, 2027 | ዝርዝር |
| የአርበኞች ቀን የአርበኞች ቀን፣ በሚያዝያ 27 የሚከበር ሲሆን፣ የፋሽስት ጣልያን መንግሥት ኢትዮጵያን ዳግም የወረረበትና ከአምስት ዓመታት የአርበኞች ተጋድሎ በኃላ ተሸንፎ የወጣበት ይህ ዕለት፣ በወራሪው ኃይል ወርዶ የነበረው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ዳግም በክብር የተሰቀለበት ነው። | ሕዝባዊ በዓልየስራ ዕረፍት | ሚያዝያ 27ረቡዕ, ሜይ 5, 2027 | ዝርዝር |
| ኢድ አል-አድሃ (ዓረፋ) ኢድ አል-አድሃ "የመሥዋዕት በዓል" ማለት ሲሆን፣ ከሁለቱ ዋና የእስልምና በዓላት ሁለተኛውና ታላቁ ነው። ከዓረፋት ቀን ማግስት ጀምሮ ይከበራል። | ሕዝባዊ በዓልየእስልምና በዓልየስራ ዕረፍት | ግንቦት 8እሑድ, ሜይ 16, 2027 * | ዝርዝር |
| መውሊድ መውሊድ የነቢዩ መሐመድ የልደት መታሰቢያ በዓል ሲሆን በኢትዮጵያና በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊም ማኅበረሰቦች ዘንድ በድምቀት ይከበራል። | ሕዝባዊ በዓልየእስልምና በዓልየስራ ዕረፍት | ነሐሴ 8ቅዳሜ, ኦገስት 14, 2027 * | ዝርዝር |
* የሚጠበቅ ቀን። የእስልምና በዓላት በጨረቃ መታየት ላይ ይመሠረታሉ፤ ተንቀሳቃሽ የኦርቶዶክስ በዓላት በባሕረ ሐሳብ ይወሰናሉ።